ራዕይ
በክልሉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጠብቀው፣ የህግ የበላይነት ተረጋግጦ በሀገራችን ብሎም በክልላችን በአርአያነት ሊጠቀስ የሚችል ተቋም ሆኖ ማየት ነው፡፡፡፡
ተልዕኮ
በክልሉ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የመንግስትና የህዝብ ጥቅሞች እንዲጠበቁ፣ በህገ መንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የህብረተሰቡን ንቃተ-ህግ በማሳደግ፣ ወንጀል ፈጻሚዎች ለህግ እንዲቀርቡና ለፈጸሙት ጥፋት በሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ እንዲሁም የዜጎችን የመደራጀት መብት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት መልካም አስተዳደርን ማስፈን ነው፡፡
እሴቶች
- የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣
- ገለልተኝነት፣
- ታማኝነት፣ ግልፀኝነትና፣ ተጠያቂነት፣
- ቀልጣፋነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተደራሽነት እና ወጪ ቆጣቢነት፣
- እኩልነትና የአልጋይነት ስሜት፣
- ውጤትና ተገልጋይነት ተኮር መሆን፣
- የተቀናጀ የፍትህ አገልግሎት፣
- ለለውጥ ዝግጁነት፡፡





